Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሃደራ አበራ መቀመጫቸውን አክራ ካደረጉ አምባሳደሮች ጋር ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአክራ የኢትዮጵያአምባሳደር ሃደራ አበራ ከሩዋንዳ አቻቸው ከዶክተር ኤሳ ኪርቦ እና ከላይቤሪያ ጉዳይ ፈጻሚ አሉ ኤ ማሳዊኪ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር ሃደራ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በዚህም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በቅርቡ ስለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ፍትሃዊና ሰላማዊ ነጻ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ስለተደረገው ዝግጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር በድንበር ምክንያት የተፈጠረውን ውዝግብ በሰላማዊና በድርድር ለመፍታት እያደረገ ስላለው ጥረት፣ የሕዳሴ ግድቡ የድርድር ሂደትና በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ውስጥ ኢትዮጵያ ፍትሃዊና ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት እንዲደረስ ለምታራምደው አቋምንም ገልጸዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ዙሪያ መኖር ስለሚገባው ትብብር የመረጃ ልውውጥ ተደርጓል።
በሌላ በኩል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተርነት የአፍሪካ እጩ ሆነው የቀረቡት ለዶክተ አርከበ እቁባይ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ተጠይቋል።
አምባሳደሮችም በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ የያዙ መሆኑና ተባብረው ለመስራትና ድጋፍ ለመስጠትም ያላቸውን ዝግጁነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.