Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለትግራይ ክልል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከልና ለሌሎች የህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ ካውንስለር ሊ ዩ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስረክበዋል።

ድጋፉ ሰባት የመተንፈሻ እገዛ የሚሰጡ መሳሪያዎች (ቬንትሌተሮች)፣ 36ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲሁም 1ሺህ 500 የህክምና አልባሳትን አካትቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የህክምና እርዳታ ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ድጋፉ የትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝና ለመደገፍ እንደሚውል ተጠቁሟል።

በኤምባሲው የኢኮኖሚና የንግድ ካውንስለር ሊ ዩ አንደተናገሩት፤ ድጋፉ ከቻይና መንግሥትና ከቻይና ኩባንያዎች የተሰባሰበ ነው።

ጎን ለጎንም ካውንስለሯ የሥራ ጊዜያቸውን ማጠናቀቃቸውን ጠቁመው ወደ አገራቸው ሲመለሱም የአገራቱ ግንኙነት እንዲጠናከር እሰራለሁ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.