Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ኢትዮጵያ የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች የሞባይል ኢንተርኔት በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችለውን የአራተኛው  ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎትን በድሬዳዋ አስጀመረ።

ፕሮግራሙን በድሬዳዋ፣አይሻና ጭሮ ከተሞች ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፆል።

ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሃገሪቱ የሞባይል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ከተሞች የማስፋፊያ ስራዎችን እያከናወነ  እንደሚገኝ ተገልጿል።

ይሄንን  አገልግሎት በድሬዳዋና በአካባቢው በሚገኙ በአይሻና በጭሮ ከተሞች አስጀምሯል።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራአስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ÷ በምስራቅ አካባቢ ለሚገኙ ከ330ሺህ በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት  ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህም የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ በሚገኝበት የሦስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅዱ  103 ከተሞችን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት  አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ÷ የሞባይል አገልግሎት አካታች በመሆኑና ከድህነት ለመውጣትና ለተሻለ ኑሮ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ድርጅቱ ከታሪፍ አንፃር ከሦስተኛው ትውልድ የአገልግሎት ታሪፍ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን  አስታውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ሪጅን ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትና በሃገር አቀፍ ደረጃ  ከ52 ሚሊየን በላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች እንዳሉት በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.