Fana: At a Speed of Life!

በማይጨው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው ከተማ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት እየተሰጠ መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የማይጨው ለምለም ካረል ሆስፒታል ገለጸ።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረእግዚአብሔር ኪሮስ እንዳሉት፤ ክትባቱ ከህክምና ባለሙያዎች በተጨማሪ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እና በዕድሜ የገፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ እየተሰጠ ይገኛል።
በሁለት ቀናት ውስጥ በከተማው በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ከ1 ሺህ 300 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባት መውሰዳቸውን ገልጸው ከነዚህ ውስጥ 300 የህክምና ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በመጀመሪያ አካባቢ የተወሰኑ ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ህዝቡ በብዛት ክትባቱን እየወሰደ መሆኑን አቶ ገብረእግዚአብሔር አስረድተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.