Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

በፕሮግራሙ መዝግያ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ፌስቲቫሉ ደማቅና የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዝግጅቱ፣ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀብት እንዳላት ያስገነዘባቸው መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፣ ይህንን ሀብት ይዘን ያለደግንበት ምክንያትን ቆም ብለን ማጤንና ሀብታችን መጠቀም አለብን ብለዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር  ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፣ ዝግጅቱን ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዝግጅቱ የሚገኘው ገቢ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል መሆኑን ሚኒስትሯ ተገልጿል፡፡

በፕሮግራሙ መዝግያ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.