Fana: At a Speed of Life!

ቡና ባንክ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዕጣ የወጣላቸውን ደንበኞቹን ሸለመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡና ባንክ “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” እና “የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሾፌሮችና ባለንብረቶች ቁጠባ” መርሃ ግብሮች ዕጣ ለወጣላቸው ደንበኞቹ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች አስረክቧል።

በሁለቱም ፕሮግራሞች የዕጣ አሸናፊ ለሆኑት ዕድለኞች፥ የአውቶሞቢሎች፣ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ፣ የዘመናዊ ሶፋዎች፣ የዘመናዊ ስልኮች ፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች እና የውሃ ማጣሪያዎችን አበርክቷል።

ቡና ባንክ ባለፉት ወራት ባካሄዳቸው ስምንት ዙሮች የዕጣ ኩፖኖችን በማዘጋጀት በባንኩ በኩል የውጭ ምንዛሬ የሚቀበሉና የሚመነዝሩ ደንበኞቹን ሲሸልም መቆየቱን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በዛሬው የሽልማት መርሃ ግብርም ለአንደኛ ዕጣ ዘመናዊ የ2020 ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል፣ ለሁለተኛ ዕጣ አምስት የውሃ ማጣሪያዎች፣ ሶስተኛ ዕጣ አምስት ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች እና አራተኛ ዕጣ አስር ዘመናዊ ሞባይል ቀፎዎችን ለባለዕድለኞች አስረክቧል።

የ9ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር በቅርቡ ተጀምሮ በሂደት ላይ ሲሆን 6ኛው ዙር የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሾፌሮችና ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር ደግሞ መካከለኛና ከፍተኛ የትራንስፖርት ተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎችን አካቶ በቅርቡ እንደሚጀመር ባንኩ ገልጿል፡፡

ከተመሰረተ 11 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በከፈታቸው 284 ቅርንጫፎቹ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.