Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጎጃም ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል።

አደጋው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ከረፋዱ 4:30 አካባቢ ከደንበጫ ወደ የመህል ቀበሌ ሸሊት ማህበራት ማዳበሪያ ለማራገፍ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ መሆኑን የወረዳው የመንገድ ደህንነት ክፍል ሀላፊ የሆነት ዋና ኢንስፔክተር ኑርልኝ ቢሻው ገልፀዋል።

በዚህም ተሽከርካሪው አሳፍሯቸው ከነበሩ የቀን ሰራተኞች መካከል የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና 12 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ደብረ ማርቆስና ደንበጫ ጤና ጣቢያ ለህክምና ክትትል መላካቸውንም ነው የተናገሩት።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሰላም አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.