Fana: At a Speed of Life!

በ500 ሚሊየን ብር የሚገነባው የድሬዳዋ ሽንሌ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከድሬዳዋ ሽንሌ በ500 ሚሊየን ብር የሚገነባው የ6 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጄክት ተጀመረ።

የመንገድ ስራው በሁለት የግንባታ ምእራፍ ተከፍሎ የሚከናወነው ይህ መንገድ በአንድ አመት ተኩል የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሏል።

መንገዱ ከዓለም ባንክ በተገኘ በጀት የከተሞች ተቋማት አቅም ግንባታ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ፕሮጄክት ዩአይ አይ ዲፒ ( UIIDP) የሚገነባ ነው።

የመንገድ ግንባታ ሥራው በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ እንደሚሰራ የከተማ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብልጀዋድ መሐመድ ተናግረዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገውን የጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታ  ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ፍጥነት እየሰራ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ገልጸዋል።

የመንገድ ግንባታው በእሸቱ የመንገድ ግንባታ ተቋራጭ እንደሚከናወን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.