ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን የ4ጂ ኤል ቲ አድቫንስ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን በሐረር፣ አወዳይና ሀረማያ ከተሞች የ4ጂ ኤል ቲ አድቫንስ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ።
ኢትዮ-ቴሌኮም በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ያስጀመረው የ4ጂ ኤል ቲ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት 67 ሺህ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን በሐረር፣ አወዳይና ሀረማያ ከተሞች ፈጣን የሞባይል ኢንተርኔት መጠቀም የሚያስችለውን የ4ጂ ኤል ቲ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀምረዋል።
አገልግሎቱ በሪጅኑ የነበረውን የኢንተርኔት ፍጥነት በ14 እጥፍ እንደሚያሻሽለውም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮ-ቴሌኮም በምስራቅ ሪጅን በድሬዳዋ፣ ጭሮና አይሻ ከተሞች የ4ጂ ኤል ቲኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በያዝነው ሳምንት ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!