Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ከተማ የ2021 የዓለም አቀፍ ራዕይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ሽልማት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ የ2021 የዓለም አቀፍ ራዕይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ሽልማት ተረከበች፡፡
የአሜሪካው ብሄራዊ ማዕከል ለምቹ መንገድ ኤፍ አይ ኤ (FIA) ከተባለ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ነው ምርጫውን ያካሄዱት።
በዋነኛነት ከተማዋ ለወጣቶች እና ተማሪዎች የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ፖሊሲ በማውጣት እና በመተግበር ላሳየችው ተምሳሌታዊ ስራ÷ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ፍጥነትን ቀንሶ በማሽከርከር እና የትራፊክ አደጋ መቀነሻ ዘላቂ መንገዶችን በመተግበር ላስመዘገበችው ለውጥ ለዚህ ሸልማት አሸናፊነት በቅታለች፡፡
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የእግረኛ መጠቀሚያ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት እና መኪና አልባ መንገዶች መርሐ ግብር በወር አንድ ቀን በመተግበር የሰዎችን አስተሳሰብ በመቀየር የመኪና መንገዶች ለወጣቶች የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ከተማዋ ለስራቸው ስራ ይህንን ዓለም አቀፍ ሽልማት ማሸነፍ መቻሏን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.