Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል በምታደርገው ጥረት ድጋፍ ታደርጋለች- አምባሳደር የቭጊኒ ተርኪንየቭጊኒ ተርኪን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል በምታደርገው ጥረት ሩሲያ የዘርፉ የሰው ሃይል አቅም ግንባታ ላይ ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭጊኒ ተርኪን ገለጹ።

ኢትዮጵያና ሩሲያ ከዚህ ቀደም የነበሩ ስምምነቶች ወደ ስራ በሚገቡበትና አዳዲስ የስምምነት ማዕቀፎችን መመስረት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር  አህመዲን መሀመድ ና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭጊኒ ተርኪን ሁለቱ ሃገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ሃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል  በምታደርገው እንቅስቃሴ ሩሲያ በሰው ሃይል አቅም ግንባታ ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም ያደረጓቸው ስምምነቶች የትብብር  ማዕቀፍ በመፍጠር በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ የ10 አመት መሪ እቅድ ጋር የሚጣጣሙ አዳዲስ ስምምነቶች እንዲደረጉ  መጠየቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.