Fana: At a Speed of Life!

በሞጣ ከተማ የእርቅና የአብሮነት ፕሮግራም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ብሄራዊ ክልልላዊ መንግስት በሞጣ ከተማ የእርቅና የአብሮነት ፕሮግራም ተካሂዷል።
የሞጣ ከተማ ከንቲባ አቶ የሸዋስ አንዱአለም ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ተፈጥሮ በነረበረው ችግር በእምነት ተቀማት፣ በንብረትና በሰው ህይወት ደርሶ በነበረው ጉዳት ሳቢያ ቅራኔ ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ከዚያን ጊዜ ወዲህም የተለያዩ የሰላም እና የአብሮነት የምክክር ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
በእርቅና የአብሮነት ፕሮግራሙ ላይ በወቅቱ ለደረሰው ጥፋት እንደመንግስት ይቅርታ ተጠይቋል፣ በእስልምና እና በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ሰፊ ውይይት ከተደረገ በሃላ እርቅና ሰላም ወርዷልም ነው ያሉት።
የሃይማኖት አባቶችም በቀጣይ በከተማዋ ለሚኖረው ሰላም ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሀጂ ሙፍቲ ዑመር እንድሪስ፣ በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤልን ክብረትና በሌሎችም የሥራ ሀላፊዎች ሰላምንና ህብረትን አብሮነትን፣ የሚያመላክቱ መልእክቶች ተላልፈዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የእርቅና የአብሮነት ፕሮግራሙ በመካሄዱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በማስረሻ ፍቅሬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.