Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ጦር አልሸባብን በመደምሰስና የሽብር ኢላማውን በማክሸፍ ቀጠናውን እያፀዳ መሆኑን ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጦር አልሸባብን በመደምሰስና የሽብር ኢላማውን በማክሸፍ ቀጠናውን እያፀዳ መሆኑን የአሚሶም ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል ዳዮመንዴ ንደገያ ገለፁ።

አዛዡ በሶማሊያ ስላለው ወቅታዊ የሠላም ማስከበር ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያይተዋል።

በምክክሩ ወቅት የመከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ÷በቀጠናው ሠላምን ለማስፈን ቅንጅታዊ አሠራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን የሶማሊያ ፀጥታ ኃይልን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የአሚሶም ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል ዳዮመንዴ ንደገያ÷ የኢትዮጵያ ጦር አልሸባብን በመዋጋት እያሳየ ያለውን ጀግንነት አድንቀው÷ ቀጣውን ሠላማዊ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመላክተዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ብ/ጄ ቡልቲ ታደሰ የፀጥታ ኃይሉ እየወሰደ ባለው ዕርምጃ አልሸባብ እየተዳከመ መሆኑ እና በተለያዩ ቀጣዎች ያቀዳቸው የሽብር ተልዕኮዎች መክሸፋቸውን በውይይቱ መዳሰሱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጦር በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ አልፎ ወደ ሶማሊያ ዘምቶ ዓለም አቀፍ አሸባሪ በሆነው አልሸባብ ላይ የኃይል ዕርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት  የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.