Fana: At a Speed of Life!

ባለሀብቶች በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በተለይም በትላልቅ ከተሞች ያለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የግል ባለሀብቶች የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ፡፡

በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ያለመው ሠላም የመኖሪያ ቤት ብድር ባንክ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ይፋ ሆኗል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ኢትያጵያውያን ቢያንስ ትንሹን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የመኖሪያ ቤቶች ያስፈልጓቸዋል፡፡

በየወቅቱ እየናረ የሚሄደው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መካከለኛ የሚባል ገቢ ላላቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ፈተና መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ የሚሰማሩ እንደ ሠላም ባንክ ዓይነት በርካታ ተቋማት ያስፈልጋሉ ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚቀጥሉት አምስት አመታት 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ያቀደው ሠላም ባንክ በዝቅተኛ እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ማዕከል እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.