Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የገጠር የገንዘብ ተቋማትን ለመደገፍ የሚውል የ26 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (ኢፋድ) እና የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የገጠር የገንዘብ ተቋማትን ለመደገፍ የሚውል የ26 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሊያደርጉ ነው፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ለገንዘብ ተቋማቱ የሚደርስ ሲሆን፥ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮውን ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ቀሪውን ደግሞ ከአውሮፓ ህብረት የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ድጋፉ በዋናነት ኮቪድ19 በግብርናው ዘርፍ ያሳደረውን ጫና ለመቅረፍና በገጠር የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ የገንዘብ ተቋማትን ለመደገፍ እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራን ለማበረታታት እንደሚውል ተገልጿል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በገጠር የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ የገንዘብ ተቋማት፣ የህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ በሚተገበረው በዚህ የገጠር የገንዘብ አቅርቦት ፕሮግራምም፥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም የአፍሪካ ቢዝነስ ኮሙዩኒቲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.