Fana: At a Speed of Life!

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ለውጥ የሚያመጡና ብቃትን የሚጨምሩ ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ የአዛዥነትና እስታፍ ኮሌጅ በቀረበው የኢትዮጵያ የሰላም ማሰልጠኛ ተቋም የካሪኩለም ክለሳ ወርክሾፕ ተካሂዷል ።
የካሪኩለም ክለሳው የምድር ሀይልን ፣ የአየር ሀይልን ፣ የባህር ሀይልንና የሳይበር ደህንነት እስትራቴጂክ አመራርን አቅም እንደሚያሳድግ ተመልክቷል ።
በዚህ ወቅት የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ለውጥ የሚያመጡና ብቃትን የሚጨምሩ እንዲህ አይነት ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከሁሉም በላይ ካሪኩለሙ በራስ አቅም የተሰራ በመሆኑ ምን ያህል ጠንካራና እምቅ አቅም በሰራዊቱ ውስጥ እንዳለ የሚያመለክት ነው ብለዋል ።
የትምህርትና ስልጠና ሪፎርሙ ከታችኛው አመራር እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ በትኩረትና በክትትል ይሰራበታልም ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የካሪኩለም ክለሳው የአየር ሀይልን ፣ የምድር ሀይልን ፣ የባህር ሀይልንና የሳይበር ደህንነትን እስትራቴጂክ አመራርን አቅም በሚሳድግ መልኩ የተዘጋጀ በመሆኑ ከሀገራችን አልፎ በአፍሪካ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.