Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ከደቡብ ሱዳን ኢታማዦር ሹም ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ሳንቲኖ ደንግ ወል ጋር በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል ፡፡
አምባሳደሩ መንግስት ትግራይ ክልልን ወደ መደበኛውን ሁኔታ ለማስመለስና መልሶ ለማቋቋም እያከናወነ ስላለው ተግባር፣ የሰብአዊ ድጋፎችን በሚመለከት፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት ፣ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ እና ኢትዮጵያ የምታደርገውን መጪው ምርጫን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጄኔራሉ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን ታሪካዊ፣ መልካም ግንኙነት እና ትብብር አድቀው ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ያበረከተችው አስተዋጽኦ የማይረሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ሃገራቸው የኢትዮጵያን ጥቅም ከሚጻረሩ ኃይሎች ጋር እንደማትተባበር ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.