Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ይርዳ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ በእነሞር እና ኤነር ወረዳ ለሚገነባው ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉራጌ ዞን እነሞር እና ኤነር ወረዳ የጉስባጃይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፡፡

በጉራጌ ዞን እነሞር እና ኤነር ወረዳ የጉስባጃይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ ነው።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን እነሞር እና ኤነር ወረዳ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ የሚገነባውን የጉስባጃይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ ስርአት ላይ እንደገለጹት የኦሮሞና የጉራጌ ህዝብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ኦቢኤን ሚዲያ የጉራጌኛ ቋንቋ እንዲለማ ስርጭት ማስጀመሩ ለህዝቦች ትስስር ማሳያ መሆኑንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

የጉራጌ ማህበረሰብ በትምህርት እንዲበለጽግ የኦሮሚያ ክልል ላደረገው ድጋፍ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው በጉራጌና በኦሮሞ ህዝብ ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ማጠናከር ከምንም በላይ ትኩረት ስለሚሻ ነው የበኩላችንን ጥረት የምናደርገው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አንድነት ይበለጽጋል ያሉት አቶ ሽመልስ ዘር እና ብሄር ሳይለይ ሀገራዊ አንድነትን እናጠናክራለን ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገሸነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንዳሉት አቃፊ በሆነው የኦሮሚያ ክልል የጉራጌ ማህበረሰብ ሰርቶ እንዲለወጥ የክልሉ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የእነሞር እና ኤነር ወረዳ ነዋሪዎች እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ የሚገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትውልድን በእውቀት ከማነጽ ባለፈ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.