Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ሚሼል ሲዲቤ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ መድኃኒቶች ኤጀንሲን (ኤ ኤም ኤ) በተመለከተ ከአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ሚሼል ሲዲቤ ጋር ተወያይተዋል ፡፡

መልዕክተኛዉ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የተያዘዉን በመድኃኒቶች፣ በሕክምና ምርቶችና በተያያዥ ቴክኖሎጂዎች ላይ ዋና ተቆጣጣሪ አካልን የማቋቋም ዕቅድ ለፕሬዝደንቷ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ከኮቪድ19 ወረርሽኝ መማር እንዳለብን እና ይህንን ተቋም ማደራጀት ለአፍሪካዉያን የተሻሻለ ጤናን እና የመድኃኒት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል ፡፡

በኮቪድ19 ክትባት ተደራሽነት ዙሪያ ከታየዉ ብሄርተኝነት እንደምንማረዉ ያሉንን ነባርና እንዲሁም አዳዲስ አህጉራዊ ተቋማትና መዋቅሮች ማጠናከር ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ፕሬዝዳንቷ ተቋማቱ ካልተጠናከሩ አፍሪካ ለወደፊቱ አደጋዎች ዝግጁ መሆን እንደማትችል አፅንዖት መስጠታቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.