Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ስታዲየም “ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል ለሚደረገው ፕሮግራም ለጊዜው ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ስታዲየም “ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል ለሚደረገው የአዲስ አበባ ወጣቶች ንቅናቄ መድረክ ለጊዜው ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄደው የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በትዕግስት፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመደጋገፍ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምስጋናውን እያቀረበ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረገው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለጊዜው ዝግ የሚሆን መንገዶች

• ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀልአደባባይ
• ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድርስ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ ጥቆማ ለመስጠት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.