Fana: At a Speed of Life!

የሼህ ሆጀሌ ቤተመንግሥት እድሳት ሊደረግለት ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የሼህ ሆጀሌ ቤተመንግሥትን ጎበኙ፡፡
ጉብኝቱንም ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ያካሄዱ ሲሆን የችግኝ ተከላ መርሃግብርም ተከናውኗል፡፡
የሼህ ሆጀሌ ቤተመንግሥት ጥንታዊ እና ብዙ ስልጣኔ ባልነበረበት ጊዜ ለከተማዋና ለአካባቢው ስልጣኔን ሲያጎናጽፍ የነበረ፤ ታሪኩ ሊነገርለት እና እንክብካቤ ሊደረግለት የሚገባ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል ።
ቤተመንግሥቱን ለትውልድ መማሪያ፣ የታሪክ መንገሪያ ስፍራ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ እድሳት እና እንክብካቤ ለማድረግ እቅድ ይዟል ብለዋል፡፡
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል ።
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለቤተመንግሥቱ እድሳት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል::
መረጃውን ያገኘነው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ነው::
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.