Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) – በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃግብር በአርሲ ዩኒቨርስቲ አካሄዱ፡፡
በመርሃግብሩ የግርብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴሩን ዶክተር ሳሙኤል ሁርቃቶን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የ14 ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ተወካዮቻቸው ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልብሳት በሚል የተጀመረው መርሃ ግብር በሁሉም የሀገሪቱ ተቋማት በስፋት ይተገበራል ያሉት ዶክተር ሳሙኤል የችግኞችን ፅድቀት ለመጨመር በምሁራን ጥናት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን በበኩላቸው እንደሀገር በሚተገበረው መርሃ ግብር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰርቶ ማሳያ ስራዎችን መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ሀሳቡን ለማስፋት እሰራለሁ ብሏል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.