Fana: At a Speed of Life!

የአዳማ-አዋሽ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) -የኢትዮ -ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር አካል የሆነው የአዳማ-አዋሽ 60 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ ተጀመሯል።
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተገኙ ሲሆን የመንገዱ ግንባታ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ ይከናወናል።
በመርሃግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መብላት ከቻልን ሌሎችን መገዳደር እንችላለን ለዚህ ደግሞ መስራት እና ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል።
ባለፈው አመት የተጀመረውን መሬት ፆም ማደር የለበትም የሚለውን ጅማሮ በዚህም አመት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ እንዲያደርግልን ደግሞ በሁሉም ክልሎች ግድቦችን መገንባት ትኩረታችን ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ለመልማት እና ለማደግ ደግሞ ሰዓቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊነት የሚያይልበት ፍሬና ቅጠሉ የረገፈ ግንዱም የተቆረጠ ቢመስልም ኢትዮጵያ የምትበለፅግበት የዛፉ ፍሬ ግን በኢትዮጵያውያን እጅ ላይ ነው ብለዋል።
ይህንን ፍሬ ደግሞ መትከል እና መንከባከብ ኢትዮጵያዊነትን ማሳደግ በአንድነት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ኢትዮጵያን ማስቀጠል እና ማበልፀግ ከኢትዮጵያዊያን ውጪ በማንም አይታሰብም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍሬውን መትከል ማለት ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል አንድነታችን ይቀጥላል ማለት ነውም ብለዋል።
በኢትዮጵያዊና ሱዳን እንዲሁም በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የመብራት መስመር ዝርጋታ በቅርቡ እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አንስተዋል።
ይህም አካባቢውን በዘመናዊ መገድ ከማስተሳሰር ባለፈ በሃይል አቅርቦት፣ በንግድ እና በሌሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፣ ይህም ኢትዮጵያ ብቸዋን ሳይሆን ከወንድም ሃገራት ጋር እንደግ የሚለው ትልምን ተግባራዊ የሚያደርግም ነው ብለዋል።
ይህ ደግሞ በኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ትብብር በመሆኑ የማስገንዘብ ስራ እንሰራለን ብለዋል።
ምንም ቢፈለግ እኛ አንድ እንሁን፣ ምንም ቢፈለግ እኛ ሰላም እንሁን፣ ኢትዮጵያ ያለምንም ጥርጥር ታድጋለች ትበለፅጋለችም ።
የሚኖሩብንን ፈተናዎች ተገዳድረን አንድ ሆነን እንቀጥል ኢልኢትዮጵያንም እናሳድግ የአፍሪካም ፈርጥ እናድርጋት ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንገዱ መገንባት ኢትዮጵያ ከ90 በመቶ በላይ የወጪና ገቢ ንግድ የምታከናውንበትን የጅቡቲ ወደብ በመሆኑ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.