Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ወቅት ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ የሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ ባለ ስድስት ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አቅርቧል።

ፓርቲዎቹ እንዲያከብሯቸው የተቀመጡት የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎች፥ ተጨባጭ የሰብአዊ መብቶች እርምጃዎች ቃል ኪዳን፣ ለሰብአዊ መብቶች በቁርጠኝነት መቆም፣ ምርጫው ለስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ማረጋገጥ፣ የሕግና ፖሊሲዎች ማሻሻያ ቃል ኪዳንን፣ የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ማረጋገጥ፣ ከግጭት ቀስቃሽ እና የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ከሐይል እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ መቆጠብ የሚሉ ናቸው።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ባለፋት የቅድመ ምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ እንደነበር ጠቅሰው የምርጫውን ፍትሀዊነት እና ተአማኒነት ለማረጋገጥ የተጠቀሱት ስድስት መብቶች ሊከበሩ ይገባል ብለዋል።

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረባቸው ስድስት የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቁርጠኝነት ሊያከብሯቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስድስቱ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎች በዝርዝር ቀርበው በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይት እንደተደረገበት የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.