Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሞያሌ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ተያዘ።

በህብረትሰቡ ጥቆማና በሻሸመኔ ፖሊስ መምሪያ ክትትል የተያዘው የውጭ ምንዛሬ ከ62 ሚሊየን ብር በላይ ነው።

በዚህም 473 ሺህ 770 ዶላር፣ 393 ሺህ 660 ዩሮ እና 39 ሺህ 675 ፓውንድ ኮድ 2 አአ B 67186 በሆነ ፒካፕ መኪና ውስጥ የተያዘው።

በሻሸመኔ ከተማ 05 በተለምዶ ሞቢል በሚባለው አካባቢ ተሽከርካሪ በረቀቅ መንገድ የውስጠኛው የፋብሪካ ብሎን ተከፍቶ የተደበቀው ገንዘብ በፖሊስ ክትትል በተደረገ ፍተሻ ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር ነው የተያዘው።

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ታምራት አበበ ለፋና እንደገለጹት÷ በተሽከርካሪው ላይ ተጨማሪ ፍተሻ ተደርጎ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የተገኘ ሲሆን ገንዘቡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ሪጅን ተቆጥሯል።

በተደረገው ቆጠራም 213 ሺህ 701 ዶላር፣ 15 ሺህ 895 ፓውንድ እና 154 ሺህ 735 ዩሮ የተገኘ ሲሆን ይህም 18 ሚሊየን 268 ሺህ 685 የኢትዮጵያ ብር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ የተያዘው ገንዘብ ምንጭና አላማውን በተደራጀ የምርመራ ቡድን እያጣራ ነውም ብለዋል ።

ህብረተሰቡ ህገወጦችን በማጋለጥ ሀገርን ለመጉዳት የተሰማሩ ሀይሎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ከጸጥታ አካላት ጋር እያደረገ ያለው ትብብር የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑም ተመላክቷል።

በኃይለየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.