Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ9 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አሶሳ ቅርንጫፍ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስመርቋል፡፡
የቀይ መስቀል ማህበር ቤኒሻንጉል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽባባው አሰጌ ማህበሩ ከሚያከናውናቸው የአደጋ ምላሽ እና የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች በተጨማሪ የመንግስት አጋዥ በመሆን ላለፉት 23 ዓመታት በክልሉ በሚገኙ ሶስቱም ዞኖችና ወረዳዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
የመጠጥ ውሃ ግንባታው በኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበር የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ መሆኑንና በ2 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ገልፀው 66 ሺህ 500 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት እንደሚችል መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ የግብርና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ሀሊፋ የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበርና የአሶሳ ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት ማህበረሰቡን ለማገዝ እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነው መሰል መልካምና ማህበረሰቡን የሚደግፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.