Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በደሴ ከተማ የ4ጂ አገልገሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የአራተኛ ትውልድ (4ጂ) ኤል᎐ቲ᎐ኢ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀመረ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ የኢንተርኔት መሠረተ ልማት በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ተደራሽ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሰሜን ምስራቅ የሚገኙ የሃገሪቱ ክፍሎች ደሴን ጨምሮ፣ በሀይቅ፣ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ላሊበላ፣ ቆቦ፣ እና ወልዲያ ከተሞች የሚገኙ 577 ሺህ ደንበኞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ እና ሌሎች ጥቂት የሃገሪቱ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረው ይህ አገልግሎት ወደ 103 የክልል ከተሞች ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።

አገልግሎቱ ከቀድሞ የ3ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት 14 እጥፍ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ሆኖ ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ የምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ አግልግሎቶችን ትርጉም ባለው መንገድ ያቀላጥፋል ብለዋል።

በ2022 ዓ.ም የ4ጂን አገልግሎት ወደ አምስተኛ ትውልድ (5ጂ) የማሳደግ ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

እንደ ኢፕድ ዘገባ በስነ-ስርዓቱ ላይ የሁዋዌ ስራ አስፈጻሚ የደሴ ከተማ የካቢኔ አባላት ፣ ባንኮች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.