Fana: At a Speed of Life!

በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህዋሃት ቡድን አባላት ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ገቡ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህዋሃት ቡድን አባላት በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል በሰሜን ዕዝ ላይ እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሰው ወደ ጎረቤት ሀገር ከሸሹ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት መካከል 1ኛ.ሀብቶም ገብረስላሴ ወልዩ፣ 2ኛ. መሰለ ታመነ እሼቱ እና 3ኛ. ኮነሬል መሀመድ በሪሁ ኑር የተባሉት የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉትን የህዋሃት አሸባሪ ቡድን አባላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪዎችን ተረክቦ ጉዳዩን በህግ አግባብ የሚያጣራ መሆኑን ገልጿል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የደህንነትና የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውን የህዋሃት አመራሮችና የጦር መኮንኖችን ከተደበቁት ስፍራ በማደን ለህግ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.