Fana: At a Speed of Life!

የሁዋዌ-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአይ ሲ ቲ ልምምድ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁዋዌ-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ (አይሲቲ) ልምምድ ማዕከል ተመርቆ ተክፍቷል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና÷ የማዕከሉ መከፈት የዩኒቨርሲቲው የአይ ሲ ቲ ተማሪዎች በቂ ክህሎት ይዘው እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል ፡፡
ይህም መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን ለማሳደግ ለጀመረው ስራ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ማቅረብ ያስችላልም ነው ያሉት፡፡
የአይሲቲውን ዘርፍ ማሳደግ ሃገሪቱ እየገነባች ላለችው የዲጂታል ኢኮኖሚ አጋዥ መሆኑንም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲዔታ ዶክተር ሙሉ ነጋ ተናግረዋል፡፡
የማዕከሉን ግብዓቶች ያሟላው ሁዋዌ፣ የዲጂታል ሽግግር ለማድረግ አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ከትላልቅ ድርጅቶች ጋር ለመስራት በር እንደከፈተለት መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.