Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክ/መንግስት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን እየሰራ ነው -አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የተተገበሩ የልማት ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው የክልሉ መንግስት ለበርካታ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም የህዝብ ተሳትፎ በማጠናከር ከተጓተቱ ፕሮጀክቶች በተጨማሪም ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም ለቀጣዮቹ አመታት ዝግጅት በማድረግ ረገድ መጠነ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተለይ በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ረገድ አበረታች ስራዎች መሠራታቸውን ያነሱት አቶ ሽመልስ 11 ሺህ1 ፕሮጀክቶችን በ 31 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ በመጨረስ ለህዝብ አገልግሎት እንዲዘጋጅ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ ሲሆኑ በ23 ቢሊየን ብር ግምት ” የዜግነት ግዴታ ” የተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።
በግብርናው ዘርፍ እንዲሁ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን በማንሳት በክልሉ በበጋ የስንዴ መስኖ 300 ሺህ ሄክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ከ382 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል ።
ከዚህም 15 እስከ 16 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ አክለው ገልፀዋል ።
የተገኙትን መልካም ውጤቶች አጠናክሮ መቀጠል እንዳለ ሆኖ የክረምት ግብርና፣የዜግነት አገልግሎት ማስቀጠል ፣የአረንጓዴ አሻራ ስራና የቀጣዩ 10 አመት እቅድ የክልሉ መንግስት ቀጣይ ትኩረቶች መሆናቸውንም ገልፀዋል በመግለጫቸው፡፡
በይድነቃቸው ኃ/ማርያም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.