Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከሚሽኑ በሰባት ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ/ም ባከናወነው ኦፕሬሽን ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮችና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦችን ይዞ ነው ምርመራ የጀመረው፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ሲያውኩ የነበሩ በተለይ የትራፊክ መብራት ካስቆመው ተሽከርካሪ ላይ ስፖኪዮ ገንጥለው እንደሚወስዱ ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ ሞባይል ስልክ ፣ የአንገት ሃብል ፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው እንደሚሰወሩ ታውቋል፡፡
በአጠቃላይ ትኩረታቸውን በዋና ዋና አደባባይ የትራፊክ መብራት በያዘው ተሽከርካሪ ላይ አድርገው ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ኮሚሽኑ ከህዝብ ከደረሰው ጥቆማና ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
በሌላ በኩልም የተሰወኑት ግለሰቦች የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውን መገለጡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በከተማው የሚስታወሉ መሰል ስጋቶችን ለመቀነስም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ህግን የማስከበር ተግባርና በተጠርጣሪዎቹ ላይ እየተደረገ ያለው ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የከተማው ነዋሪም ለሰላም ስጋት የሆኑ ግለሰቦችን በመጠቆምና ማስረጃ በመሆን ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.