Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 2 ሺህ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ያህል ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኞች የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

እንደኢዜአ ዘገባ የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያገኙት በብሎክ አደረጃጀት የተመረጡ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውም ታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር አባይ፥ አካል ጉዳተኞችን ማገዝ፣ መርዳትና የተለያዩ ህጎችና ፖሊሲዎችን ቀርፆ መስራት የመንግስት ድርሻ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም በመንግስት በኩል እየተሰሩ ያሉ ጅምር እንቅስቃሴዎችን ለማስፋት የተለያዩ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.