Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በፌዴሬሽን ምክር ቤት የዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ የህገ-መንግስት አስተምህሮና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ÷ የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ የህገ-መንግስት አስተምህሮና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅትም ቋሚ ኮሚቴው በክልሉ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ድጋፎችን ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመሬት የወሰን ጉዳይ ላይ ህግና ስርአትን ተከትሎ ህዝብን መሰረት በማድረግ በአስቸኳይ ምላሽ በሚያገኝበት ዙሪያም መክሯል።

አሁን ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያትም ክልሉ አስፈላጊውን ገቢ ለማግኘት አዳጋች በመሆኑም ችግሩን በማየት የክልሉን በጀት በልዩ ሁኔታ መመደብ በሚቻልበት ሁኔታም መክሯል።

በክልሉ ፀጥታና ደህንነት ጉዳይ እንዲሁም ተፈናቃዮችን አስፈላጊው ሂደት ተሟልቶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንደሚሰራም ከቋሚ ኮሚቴው ጋር በተደረገው ውይይት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በተመሳሳይ ዜና ዋና ስራ አስፈጻሚው የአክሱምና የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ስራ ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት አመራሮች ጋር መክረዋል።

በዚህ ውይይት ላይም በተለይም የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያ በቅርቡ ወደ ስራ እንዲመለስ እንደሚደረግ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን፣ የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ደግሞ አስፈላጊው የጥገና ስራ እንደሚከናወንለት መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.