Fana: At a Speed of Life!

በሶስት የአሜሪካ ግዛቶች ከሚገኙ የዲያስፖራ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

 

በሶስት የአሜሪካ ግዛቶች ከሚገኙ የዲያስፖራ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢንዲያና፣ ሚቺጋን እና ኦሃዮ ግዛቶች ከሚገኙ የዲያስፖራ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

በወቅታዊ ጉዳይ እና የህዳሴ ግድብ ድጋፍን አስመልክቶ በኢንዲያና፣ ሚቺጋን እና ኦሃዮ ስቴቶች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የቦርድ አመራሮች ፣አባላት እና ከልዩ ልዩ የማህረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም በተለይ በአሁኑ ሰዓት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በህወኃት የሽብር ቡድን ላይ የተወሰደውን የህግ ማስከበር አርምጃ ምክኒያት በማድረግ በአንዳንድ አገሮች እና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በአገራችን ላይ እየተደረገ ያለውን ተገቢነት የሌለው ጫና በጋራ ሆኖ በተለያዩ መንገዶች መመከት እንደሚገባ ከመግባባት ተደርሳል።

በዲያስፖራው በኩል በተለይም በአገሩ ዜግነት ባለው እና መራጭ የሆነው የማህበረሰብ ክፍል ትክክለኛውን እውነታ ለሴናተሮችም ሆነ ለሌሎች ተመራጮች በማስረዳት ወገናዊ ግዴታውን መወጣት እንደሚገባው ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ለታላቁ የህዳሴው ግድብ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በሚኒሶታ ከኢትዮጵያ ከቆንስላ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.