Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ለአርብቶ አደር አከባቢ 50 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 50 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን የኦሮሚያ አርብቶ አደር አካባቢ ልማት አስተባባሪ ኮምሽን አስታውቋል።

ኮምሽነር ሮባ ቱርጬ፥ በዚህ አመት በክልሉ በ645 ሚሊዮን 862 ሺህ 859 ብር ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጅክቶች ተገንብተዋል ብለዋል፡፡

የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በውሃ ሀብት ልማት ላይ በማተኮር እየተሰራ ነውም ብለዋል ኮምሽነሩ።

በ2013 ዓ.ም በበጋው ወቅት የውሃ እጥረት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች አርብቶ አደሩ የክረምቱን የዝናብ ውሃ በማጠራቀም እንዲጠቀም 23 ኩሬዎች ፣8 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች እና  6 ውሃ ማቆሪያ ኩሬዎች መዘጋጀታቸውን አቶ ሮባ ገልፀዋል።

ምንጭ፡- ኦቢኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.