Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስራ የአባይ ጉዳይን ከፊት ያስቀደመ ነው- ምሁራን

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስራ የአባይ ጉዳይን ከፊት ያስቀደመ መሆኑን በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ ውይይት ላይ ተገለጸ።
የህዳሴ ግድብ አሁናዊ ሁኔታ የውጭ ጣልቃ ገብነት፤ የሳይንስ ዲፕሎማሲ እና የምሁራን ሚና በሚል አርእስት በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የውይይት መድረክ ጥናታዊ ፅሁፍችም ቀርበዋል።
በአባይ ወንዝና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በርካታ ጥናቶችን እየሰሩ የሚገኑት በአባይ ወንዝ ተመራማሪ እና ተደራዳሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ የህዳሴው ግድብ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ያዕቆብ በጥናታዊ ፅሁፋቸው እንዳመላከቱት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስራ የአባይ ጉዳይን ከፊት ያስቀደመ ነው ሲሉ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት የሚያነሱት የግድቡ የበላይ እንሁን አካሄድ ከድርድር የማይቀርብም ነው ብለዋል።
የአባይ ወንዝ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አምባሳደር ኢብራሂም ኢድሪስ ኢብራሂም በህዳሴው ግድብ ድርድር ህጋዊ ማእቀፍ በሚል አርእስት ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የግብፅ እና ሱዳን ዲፕሎማቶች የሚያነሱት መደራደሪያ ሀሳብ የኢትዮጵያን በራስ ሀብት የመጠቀም መብትን የሻረ እና በጋራ የመጠቀም መብትን የማያከብር በመሆኑ ኢትዮጵያ ልትቀበለው አትችልም ብለዋል።
አምባሳደር ኢድሪስ ኢብራሂም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተደጋጋሚ የሚያነሷቸው ሀሳቦች የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ያለሙ እና ከድርድር ያፈነገጡ ስልታዊ መንገዶችን ሲጠቀሙ ቆይተዋል ሲሉ ኢትዮጵያ የድርድሩን ምእራፍ እና የግንባታው ሂደትን በማጠናከር ትቀጥልበታለች ሲሉ ተናግረዋል።
የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ተደራዳሪ የቴክኒክ ቡድን መሪ እና ሰብሳቢ እንዲሁም በውሃ መስኖና ኢነርጂ የሚኒስትሩ አማካሪ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፥ በዙም መተግበሪያ የህዳሴው ግድብ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ግድቡ ኢትዮጵያዊን ወደማይቀለበስበት ደረጃ አድርሰውታል ብለዋል።
የግንባታ ሂደቱ በሶስት ደረጃ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ግድቡ አሁን ከ80 በመቶ በላይ ተጠናቋል ሲሉ ሁለተኛው ሙሌት ሲጠናቀቅ 18 ነጥብ 4 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዮብ ውሃ መሸከም ስለሚችል ግድቡ ራሱን በሚጠብቅበት ደረጃ ይደርሳል ብለዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.