Fana: At a Speed of Life!

ለስምንት ዓመት የተጓተተው ግድብ 70 በመቶ ላይ ደረሰ – ዐቢይ አህመድ

 አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለስምንት ዓመት የተጓተተው የመገጭ ግድብ 70 በመቶ ላይ ደረሰ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፕሮጅክቱ አፈጻጸም የተሰማቸውን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
የግድቡ ግንባታ እጅግ በመጓተቱ ሕዝብ እንዲማረር ያደረገ፣ ሀገርን ያከሰረ ፕሮጀክት እንደነበር እና መንግስት ባደረገው ክትትል ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል ሲሉም አክለዋል።
በቀጣዮቹ አምስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ ለጎንደር መጠጥ ውኃ እና ለመስኖ ልማት ይውላል።
በጉብኝቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውም ተሳትፈዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.