Fana: At a Speed of Life!

ኮንዶር ኤሌክሮኒክስ በኢትዮጵያ የቅደመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማካሄድ ተስማማ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ ግዙፉ የኤልክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ኮንዶር በኢትዮጵያ የቅደመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማካሄድ ተስማማ።

በአልጄሪያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የኤሌክትሪክ ከኩባንያው የስራ ሃላፊዎች ጋር በመገናኘት እንዲሁም የመስክ ጉብኝት በማድረግ በአገራችን ስለሚገኙ የኢንቨስትመንት እድሎችን በተመለከተ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኤልክትሮኒክስ ኢንዱስትሪ መስክ ያልተነካ ከፍተኛ የኢንቬስትመንት እድል መኖሩን የገለጹት አምባሳደሩ፣ መንግስት በዘርፉ ለሚሰማሩ የውጭ ድርጅቶች የተለያዩ የኢንቬስትመንት ማበረታቻ ጥቅሎች ማዘጋጀቱን አሰረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት እንደ ኮንዶር ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ቢሰማሩ በቀጣናው ከሚገኘው ከፍተኛ የገበያ እድል ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

የኩባንያው መስራችና የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሁሴን ቤንሃማዲ፥ በኢትዮጵያ የሚገኘውን የኢንቬስትመንት እድል ብሎም እየተመዘገበ የሚገኘውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ አድናቆት እንደሚመለከቱት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና አልጄሪያ ወንድማማች ሀገሮች መካከል የተጠናከረ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲፈጠር ድርጅታቸው ኮንዶር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ማስታወቃቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.