Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ዛሬ ይመረቃሉ

 
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የተገነቡ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ዛሬ ይመረቃሉ።
 
24 የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በድምሩ 37 ነጥብ 6 ኪሜ በላይ ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ከ6 እስከ 40 ሜትር የጐን ስፋት አላቸው።
 
በዛሬው ዕለት በይፋ ከሚመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከመገናኛ – ወረዳ 17 ጤና ጣቢያ፣ ቦሌ ወረዳ 12 – ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም እና ሽሮ ሜዳ – ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት መንገድ ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.