Fana: At a Speed of Life!

ለሴካፋ ውድድር ዝግጅት ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ተጫዋቾች ጥሪ  ተደረገ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዝግጅት ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ።

ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት የእግርኳስ ውድድር ከሰኔ 26፣2013 እስከ ሐምሌ 11፣2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ እየተመራ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል።

ወደ አፍሪካ ዋንጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲያልፍ የቡድኑ አባላት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል እድሜያቸው በብሔራዊ ቡድኑ እንዲካተቱ የሚፈቅድላቸው 5 ተጫዋቾች በዚህ ምርጫ የሚካተቱ ሲሆን፣ ቡድኑ ልምምድ ከጀመረ ሰባት ቀናት በኋላ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ የተገለፀ ሲሆን ከሁሉም የፕሪምየር ሊግ እና ከ4 ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ምርጫው  ስለመከናወኑ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.