Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የማሰሮ ደንብ ትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ አስጀመሩ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

የደጅ አዝማች ብሬ ዘገዬ መታሰቢያ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ነው የመሠረተ ድንጋይ ያስቀመጡት።
በስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚነስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን፣ ርእስ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገተኝተዋል።
ቀደማዊት እመቤቷ በአማራ ክልል ከአሁን ቀደም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስገንብተው ያስመረቁ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.