Fana: At a Speed of Life!

ለመንገድ ጥገና የሚውሉ የግንባታና የጥገና ማሽነሪዎች ለክልሎች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመንገድ ፈንድ ለክልል የመንገድ ኤጀንሲዎች በስድስት መቶ ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ ማሽነሪዎችን ለክልሎች አከፋፈለ።
በዛሬው እለትም የደረሱትን 21 የግንባታና የጥገና ማሽነሪዎች ለክልሎቹ የተላልፉ ሲሆን ተጨማሪ 12 ማሽነሪዎች በቅርቡ ይሰጣሉ ተብሏል።
ርክክብ የተፈጸመባቸው ሞተር ግሬደሮች ክልሎች በአግባቡ ከተጠቀሙበት በከፊል የመንገድ ብልሽትን ለመጠገንና ለአዳዲስ ግንባታም አጋዥ መሆን ይችላሉ።
የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት እስከአሁን ከ23 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ 500 ሺ ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና አድርጓል።
ጽ/ቤቱ በቀጣዮቹ አስር አመታት አቅዶ እየከወናቸው ላሉ የለውጥ ስራዎች የሚያግዙትን ተግባራት እየፈጸመ ሲሆን አመታዊ ገቢንም አሁን ካለበት 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ወደ 14 ቢሊየን ብር ለማድረስ አቅዳል።
በዚህም የጀመረውን የክልል መንገድ ኤጀንሲዎች የመደገፍ ተግባር ያሳድገዋል ተብሏል።
በርክክብ ስነስርአቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራና የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሀይለየሱስ ስዩም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.