Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትውልድ ኢትዮጵያዊቷ በዜግነት ሆላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን በ10ሺህ ሜትር ሴቶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን ሰበረች ::
አትሌቷ በጀረንጆቹ 2016 በኢትዮዽያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረውን ርቀት በማሻሻል ነው አዲስ የዓለም ክብረወሰን የሰበረችው፡፡
በዚህም በ2016 በአትሌት አልማዝ አያና በ29 ደቂቃ 17 ሰከንድ በ45 ማይክሮ ሰከንድ ተይዞ የነበረውን ርቀት ዛሬ በኔዘርላንድ ሄንጌሎ በተካሄደው ውድድር በ 29 ደቂቃ 6 ሰከንድ 82 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገብ ችላለች።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.