Fana: At a Speed of Life!

ችግኝ እየተከሉ ሃገርን ውብ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ችግኝ እየተከሉ ሃገርን ውብ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል የ2013 ዓ.ም የ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስጀምረዋል።

ኢትዮጵያን ማልበስ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከወዲሁ ውጤት እየተመዘገበበት ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የየክልል ርዕሳነ መስተዳድራን ተገኝተዋል።

በዛሬው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሃገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል።

በ3ኛው ዙር መርሃ ግብር እንደክልል 1 ነጥብ 83 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን፥ ሃምሌ 8 ቀን በአንድ ጀንበር 247 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል።

የሚተከሉ ችግኞች የት እንደሚተከሉ የመከታተያ ስርዓት የተዘረጋ ሲሆን፥ ለዚህም 35 ሺህ ሄክታር መሬት ተለይቷል ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም በክልሉ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ተተክሎ 65 በመቶ የጽድቀት መጠን እንዲሁም ባለፈው አመት 1 ነጥብ 57 ቢሊየን ችግኞች ተተክለው 78 በመቶ የጽድቀት መጠን እንደነበረው ተገልጿ፡፡

በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 16 ሚሊየን የፍራፍሬ ችግኞች ይተከላሉ።

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.