Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን 1 ሚሊየን 80 ሺህ ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ኮድ 3 የሆነ የጭነት መኪና እቃዎቹን ይዞ ከባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ሲጓጓዝ ነው በህብረተሰብ ጥቆማና በጸጥታዉ አባላት ክትትል የተያዘው፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ግምቱ 900 ሺህ ብር የሆነ ልባሽ ጨርቅና 12 ኩንታል ህገ ወጥ ቡና መሆኑ ታውቋል፡፡
የአዳባ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የአከባቢ ጸጥታ አስከባሪ ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጅን ሀጂ ጎበና የህዝብ ተሳትፎ የህገ-ወጥ ንግዶችን ለመከላከል አስዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወረዳዉ በየጊዜዉ ከሌላ ቦታ የሚጓጓዙ ህገ-ወጥ ንግዶች ስለሚበረቱ በትኩረት እየተሰራ ነዉ ተብሏል፡፡
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.