Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የምግብ ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው የሸጡ 24 ድርጅቶች እርምጃ ተወሰደባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የምግብ ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ሲሸጡ በተገኙ 24 ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታውቀ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ “ዛሬ ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ ለነገ ጤና” በሚል መሪ ሃሳብ የዓለም የምግብ ደህንነት ቀን ዛሬ ተከብሯል።

የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ የበአሉ መከበር የምግብ ወለድ በሽታዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በሽታው ሲከሰትም በቀላሉ ለመለየት እንዲሁም የከፋ ችግር ሳያስከትል ለመቆጣጠርና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በዋናነት ስጋት የሆነው ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር በመደባለቅ ለገበያ ማቅረብ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከባዕድ ነገር ጋር በመደባለቅ ለገበያ እየቀረቡ ካሉ ምግቦች መካከል እንጀራ፣ ቅቤ፣ በርበሬና ማር እንደሚገኙበትም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምግቦቹ ወቅት ጠብቀው ለገበያ እንደሚቀርቡ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፥ “የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተደረገ ክትትል በአዲስ አበባ 24 ድርጅቶች ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው በመገኘታቸው ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል” ብለዋል።

በአራት ክፍለ ከተሞች በተደረገ ክትትል 3 ሺህ 360 ኪሎ ግራም ቅቤ፣ 480 ኩንታል በርበሬ እና ከ1 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ከቅቤ ጋር ለማደባለቅ የሚውሉ የአትክልት ቅቤና የፓልም ዘይት መያዙን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.