Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የፌስ ቡክ ገጽ ከፍተኛ ተሳትፎ ካላቸው ገጾች አንዱ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጠቅላይ ሚንስትር  ዐቢይ አህመድ የፌስ ቡክ ገጽ ከፍተኛ ተሳትፎ እና መስተጋብር የሚያሳዩ የአለም መሪዎች ገጽ አንዱ እንደሆነ ተገለፀ።
ፌስቡክን ከሚጠቀሙ የሀገራት መሪዎች ውስጥ በተለየ ሁኔታ ገጻቸው በተሳታፊዎች Interaction (መስተጋብር) መጠን ሲለካ ከፍተኛ የሆነው አፍሪካዊው መሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እንደሆኑ ትዊፕሎማሲ የሚባለው ታዋቂ አወዳዳሪ ድረገጽ አስታወቀ ።
በአፍሪካ ካሉት መሪዎች ውስጥ በአንደኝነት የተቀመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሲሆኑ ሃመድ ባካዮኮ ከኮትዲቯር ፣ አብዱልፈታ አልሲሲ ከግብጽ ፣ ናንአኩፎ አዶ ከጋና እና ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከዩጋንዳ እስከ አምስተኛ ያሉ ደረጃዎችን ይዘዋል።
በሌላ በኩል የፌስቡክ ገፅ በየጊዜው በሚያወጣው የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎች ዝርዝር ደረጃ መሠረት ከአፍሪካ መሪዎች በሳምንት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ (Engagment) የታየበት የፌስቡክ ገጽ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ  አሊ የፌስ ቡክ ገፅ እንደሆነም አሳይቷል።
በዚህ የተሳትፎ (Engagment) ንጽጽር በሰፊ ልዩነት በ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ከአናት የተቀመጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፌስቡክ ገጽ ከሁሉም መሪዎች በልዩ ሁኔታ የተለያዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሃሳቦች እና ተግባራት በወቅቱ ለህዝብ ግልፅ በማድረጉ፣ በወቅታዊ መልዕክቶች ታጅቦ በመቅረቡ፣ በሚያማምሩ እና ተስፋን በሚጭሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ክንውኖችን በማቅረቡ እንደሆነ የተለያዩ ድረገፆች እየገለፁ ይገኛሉ።
የጠቅላይ ሚንስትር ፌስቡክ ገፅ ወደ 3 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚጠጋ ተከታይ ያለው ሲሆን ፤ በተለያየ መልኩ ህዝብን ከመሪ የማገናኛ ቁልፍ የተግባቦት ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
የጠቅላይ ሚንስትሩ የፌስ ቡክ ገፅ የተለያዩ መረጃዎችን በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በማቅረብ ከአንድ አመት ተኩል በላይ አስቆጥሯል።
ምንጭ:- ጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.