Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ያሉ ቱባ ባህሎች ያጋጠሙ ግጭቶች እንዲፈቱ ትልቅ ድርሻ ነበራቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ያሉ ቱባ ባህሎች በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ግጭቶች እንዲፈቱ ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው ተግልጿል።
የሰላም ሚኒስቴር ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር ከታህሳስ እስከ ግንቦት ወር ሲያካሄድ የቆየው የማህበረሰብ ተኮር የውይይት ማጠቃለያ መድረክ በአርባ ምንጭ ተካሄደ።
በሰላምና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲኖር ሁሉም የበኩሉን መወጣት ይጠበቅበታል ያሉት የመድረኩ ተሳታፊ አባቶች÷ የሰላም ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ማህበረሰብ አቀፍ ምክክሮች ማድረጉ ያስመሰግነዋል ብለዋል።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብረሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የበርካታ ባህልና እሴቶች ባለቤት ብትሆንም ከጊዜ በኋላ በመጣው አለመደማመጥ ለዘመናት የተገነባውን የሠላም እሴት የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ነው ያሉት።
ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውን የሠላም እና የመቻቻል እሴት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲህ አይነት የማህበረሰብ ውይይት ያስፈልጋል ብለዋል።
የጋሞ አባቶች ስለሰላም ባላቸው ጠንካራ አስተሳሰብና ባህል ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በማድረግ አራአያነት ያለው ተግበር መስራታቸውን አስታውሰዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስባባሪ እና የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ÷በደቡብ ክልሉ ያሉ ቱባ ባህሎች የሠላም እሴቶችና የምክክር ባህል በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ግጭቶች እንዲፈቱ አስችለዋል ነው ያሉት ።
አዲሱ የሰላም ግንባታ ፖሊሲ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማቀፍ በዜጎችና በመንግሥት መካከል ያለውን የመተማመን እና የግኑኝነት ደረጃ የሚያሻሽል ብለዋል።
በክልል በየደረጃው በተደረጉ ውይይቶች በርካታ ለውጦች እንዳመጡና የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በጎ አስተዋጾ እንደነበራቸው አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.