Fana: At a Speed of Life!

ብርሃን ባንክ የሞባይል ፖስ ስርዓትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ብርሃን ባንክ ከሳንቲም ፔይ ኢንጂነሪንግ ጋር በመሆን ሞባይል ፖስ የተሰኘ በተንቀሳቃሽ የመክፈያ መሳሪያ አማካኝነት ከፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ስርዓት ይፋ አደረገ::
ስርዓቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡
ይህን አስመልክቶም ባንኩ ከሳንቲም ፔይ ኢንጅነሪንግ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫው የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ይህ የመክፈያ መሳሪያ ለትግበራ ከመቅረቡ በፊት የክፍያ ስርዓቶቹ እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ስለማሟላቱ በሚመለከተው መስሪያ ቤት የደህንነት ምርመራ ተደርጎለት በማለፉ ወደ ትግበራ እንደገባ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ የመክፈያ መሳሪያው ከተለያዩ የስማርት አንድሮይድ ስልኮች ጋር በመገናኘት የሚሰራ ከመሆኑም ባሻገር ተመሳሳይ አገልግሎት ከሚሰጡ መሳሪያዎች አንጻር ፈጣን መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመግለጫው እንደተገልጸው ደንበኞች መሳሪያዎችን በመጠቀም የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ማለትም የውሃ፣ የስልክ፣ የኢንተርኔት፣የዲ ኤስ ቲቪ እና ሌሎች ክፍያዎችን መፈጸም እንደሚያስችላቸው ታውቋል ።
በተጨማሪም ደንበኞች መሳሪያዎቹን በመጠቀም ከማናቸውም የኤቲኤም ካርዶች ገንዘብ መቀበል የሚችሉ በመሆኑ የእጅ በእጅ የገንዘብ ሽያጭን በማስቀረት ግብይትን ከወረቀት ገንዘብ ነጻ ለማድረግ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኗል::
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.