Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኡሑሩ ኬንያታን የቴሌኮም ፍቃድ ስምምነትን በምንፈራረምበት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እና 1 ቢሊየን ችግኞችን ለጎረቤት ሃገር በማዘጋጀት የ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ወደ ቀጣናው በምታስፋፋበት ወቅት ላይ ነን ሲሉም ተናግረዋል።
ይህንን መሠረት በማድረግም ችግኞችን በጋራ መትከላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.